-
ዘዳግም 12:29-31አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 “ከምድራቸው የምታስለቅቃቸውን ብሔራት አምላክህ ይሖዋ ሲያጠፋቸውና+ በምድራቸው ላይ ስትኖር 30 እነሱ ከጠፉ በኋላ በእነሱ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። ‘እነዚህ ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩ የነበረው እንዴት ነው? ቆይ እኔም እንደ እነሱ አደርጋለሁ’ ብለህ ስለ አማልክታቸው አትጠይቅ።+ 31 አንተ በአምላክህ በይሖዋ ላይ ይህን ማድረግ የለብህም፤ ምክንያቱም እነሱ ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ሁሉ ለአማልክታቸው ያደርጋሉ፤ ሌላው ቀርቶ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአማልክታቸው በእሳት ያቃጥላሉ።+
-