-
ኤርምያስ 27:8-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 “‘“‘የትኛውም ብሔር ወይም መንግሥት የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን ለማገልገል ፈቃደኛ ባይሆን እንዲሁም አንገቱን በባቢሎን ንጉሥ ቀንበር ሥር ለማስገባት እንቢተኛ ቢሆን ያንን ብሔር በእሱ እጅ ፈጽሞ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍ፣+ በረሃብና በቸነፈር* እቀጣዋለሁ’ ይላል ይሖዋ።
9 “‘“‘ስለዚህ “የባቢሎንን ንጉሥ አታገለግሉም” የሚሏችሁን በመካከላችሁ ያሉትን ነቢያት፣ ሟርተኞች፣ ሕልም አላሚዎች፣ አስማተኞችና መተተኞች አትስሙ። 10 የሚተነብዩላችሁ ነገር ሐሰት ነውና፤ እነሱን የምትሰሙ ከሆነ ከምድራችሁ ተፈናቅላችሁ ወደ ሩቅ ቦታ ትወሰዳላችሁ፤ እኔም እበትናችኋለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።
-