የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 1:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን ፈልጉ፤+

      ጨቋኙ እንዲታረም አድርጉ፤

      አባት የሌለውን ልጅ* መብት አስከብሩ፤

      ለመበለቲቱም ተሟገቱ።”+

  • ኤርምያስ 7:5-7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ 6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ 7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’”

  • ኤርምያስ 22:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለፍትሕና ለጽድቅ ቁሙ። የተዘረፈውን ሰው ከአጭበርባሪው እጅ ታደጉ። ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አታንገላቱ፤ አባት የሌለውን ልጅ* ወይም መበለቲቱን አትበድሉ።+ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።+

  • ሕዝቅኤል 22:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 የምድሪቱ ሰዎች የማጭበርበር ድርጊት ፈጽመዋል፤ ሌሎችን ዘርፈዋል፤+ ችግረኛውንና ድሃውን በድለዋል፤ ደግሞም ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው አጭበርብረዋል፤ ፍትሕንም ነፍገውታል።’

  • ሚክያስ 2:2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  2 እርሻን ይመኛሉ፤ ነጥቀውም ይይዙታል፤+

      ቤቶችንም ይመኛሉ፤ ደግሞም ይወስዳሉ፤

      የሰውን ቤት፣

      የሰውንም ርስት አታለው ይወስዳሉ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ