49 ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን+ እንዲህ ይላል፦
“እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም?
ወራሽስ የለውም?
ታዲያ ማልካም፣+ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው?+
ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?”
2 “‘ስለዚህ እነሆ፣ አሞናውያን በሚኖሩባት በራባ+ ላይ
የጦርነት ማስጠንቀቂያ ድምፅ የማሰማበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።
‘የፍርስራሽ ቁልል ትሆናለች፤
በእሷም ሥር ያሉት ከተሞች በእሳት ይቃጠላሉ።’
‘እስራኤልም የቀሙትን መልሶ በእጁ ያስገባል’+ ይላል ይሖዋ።