ዘዳግም 28:49 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 2 ነገሥት 24:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በኢዮዓቄም ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ምድሪቱን ወረረ፤ ኢዮዓቄምም ለሦስት ዓመት የእሱ አገልጋይ ሆነ። ሆኖም ሐሳቡን ለውጦ ዓመፀበት። 2 ከዚያም ይሖዋ የከለዳውያንን፣+ የሶርያውያንን፣ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ወራሪ ቡድኖች ይልክበት ጀመር። ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት+ ይሁዳን እንዲያጠፉ እነዚህን ቡድኖች ይልክባቸው ነበር። 2 ነገሥት 25:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ሠራዊቱን ሁሉ አስከትሎ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ።+ በዙሪያዋም ሰፈረ፤ ደግሞም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ቆለለ፤+
24 በኢዮዓቄም ዘመን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ምድሪቱን ወረረ፤ ኢዮዓቄምም ለሦስት ዓመት የእሱ አገልጋይ ሆነ። ሆኖም ሐሳቡን ለውጦ ዓመፀበት። 2 ከዚያም ይሖዋ የከለዳውያንን፣+ የሶርያውያንን፣ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ወራሪ ቡድኖች ይልክበት ጀመር። ይሖዋ አገልጋዮቹ በሆኑት በነቢያት አማካኝነት በተናገረው ቃል መሠረት+ ይሁዳን እንዲያጠፉ እነዚህን ቡድኖች ይልክባቸው ነበር።
25 ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ በአሥረኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር+ ሠራዊቱን ሁሉ አስከትሎ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ።+ በዙሪያዋም ሰፈረ፤ ደግሞም በዙሪያዋ የአፈር ቁልል ቆለለ፤+