10 እኛ ግን አምላካችን ይሖዋ ነው፤+ እሱንም አልተውነውም፤ የአሮን ዘሮች የሆኑት ካህናት ይሖዋን እያገለገሉ ሲሆን ሌዋውያንም በሥራው ይረዷቸዋል። 11 በየጠዋቱና በየማታው+ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ያቀርባሉ፤ የሚነባበረውም ዳቦ+ ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ይቀመጣል፤ የወርቁን መቅረዝና+ መብራቶቹን በየማታው ያበራሉ፤+ ምክንያቱም እኛ በአምላካችን በይሖዋ ፊት ያለብንን ኃላፊነት እየተወጣን ነው፤ እናንተ ግን እሱን ትታችሁታል።