3 እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከልሽ ደም የምታፈሺ፣+ ፍርድ የምትቀበዪበት ጊዜ የደረሰብሽ፣+ ትረክሺም ዘንድ አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶች የምትሠሪ ከተማ ሆይ፣+ 4 ያፈሰስሽው ደም በደለኛ አድርጎሻል፤+ ደግሞም አስጸያፊ ጣዖቶችሽ አርክሰውሻል።+ የቀኖችሽን መጨረሻ አፋጥነሻል፤ የዘመኖችሽም መጨረሻ ደርሷል። ስለዚህ ብሔራት ነቀፋ እንዲሰነዝሩብሽ፣ አገሩም ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ።+