የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 11:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል። 12 ለብሔራት ምልክት* ያቆማል፤ በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያንም መልሶ ያመጣቸዋል፤+ እንዲሁም የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ይሰበስባል።+

  • ኤርምያስ 30:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “አንተም አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ” ይላል ይሖዋ፤

      “እስራኤል ሆይ፣ አትሸበር።+

      አንተን ከሩቅ አገር፣

      ዘርህንም ተማርኮ ከተወሰደበት ምድር እታደጋለሁና።+

      ያዕቆብ ይመለሳል፤ ሳይረበሽም ተረጋግቶ ይቀመጣል፤

      የሚያስፈራቸው አይኖርም።”+

      11 “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል ይሖዋ።

      “አንተን የበተንኩባቸውን ብሔራት ሁሉ ግን ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤+

      ይሁን እንጂ አንተን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም።+

      በተገቢው መጠን እገሥጽሃለሁ* እንጂ

      በምንም ዓይነት ሳልቀጣ አልተውህም።”+

  • ሕዝቅኤል 34:13, 14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ከሕዝቦች መካከል አወጣቸዋለሁ፤ ከየአገሩም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች፣ በየጅረቱ ዳርና በምድሪቱ ላይ በሚገኙት መኖሪያ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።+ 14 ጥሩ በሆነ መስክ ላይ አሰማራቸዋለሁ፤ ከፍ ያሉት የእስራኤል ተራሮችም የግጦሽ መሬት ይሆኗቸዋል።+ በዚያም ጥሩ በሆነ የግጦሽ መሬት ላይ ያርፋሉ፤+ በእስራኤልም ተራሮች ላይ በለመለመ መስክ ይሰማራሉ።”

  • አሞጽ 9:14, 15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ከሕዝቤ ከእስራኤል የተማረኩትን ሰዎች መልሼ እሰበስባለሁ፤+

      እነሱም የወደሙትን ከተሞች መልሰው በመገንባት ይኖሩባቸዋል፤+

      የወይን ተክል ተክለው የወይን ጠጁን ይጠጣሉ፤+

      አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።’+

      15 ‘በምድራቸው ላይ እተክላቸዋለሁ፤

      ከሰጠኋቸውም ምድር ላይ

      ዳግመኛ አይነቀሉም’+ ይላል አምላክህ ይሖዋ።”

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ