2 ዜና መዋዕል 33:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በተጨነቀም ጊዜ ሞገስ እንዲያሳየው አምላኩን ይሖዋን ለመነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ። 13 ወደ እሱ አጥብቆ ጸለየ፤ እሱም ተለመነው፤ በእሱ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያቀረበውንም ልመና ሰማው፤ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ንግሥናው መለሰው።+ ከዚያም ምናሴ፣ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አወቀ።+ መዝሙር 25:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በወጣትነቴ የሠራኋቸውን ኃጢአቶችና በደሎች አታስብብኝ። ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩነትህ ስትል+እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን አስበኝ።+ ኢሳይያስ 43:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ስለ ራሴ ስል+ በደልህን* እኔ ራሴ እደመስሰዋለሁ፤+ኃጢአትህንም አላስታውስም።+
12 በተጨነቀም ጊዜ ሞገስ እንዲያሳየው አምላኩን ይሖዋን ለመነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ። 13 ወደ እሱ አጥብቆ ጸለየ፤ እሱም ተለመነው፤ በእሱ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያቀረበውንም ልመና ሰማው፤ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ንግሥናው መለሰው።+ ከዚያም ምናሴ፣ ይሖዋ እውነተኛ አምላክ እንደሆነ አወቀ።+