-
ዘፀአት 13:17, 18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አምላክ ምንም እንኳ አቋራጭ ቢሆንም ወደ ፍልስጤማውያን ምድር በሚወስደው መንገድ አልመራቸውም። ምክንያቱም “ሕዝቡ ጦርነት ቢያጋጥመው ሐሳቡን ለውጦ ወደ ግብፅ ሊመለስ ይችላል” በማለት አስቦ ነበር። 18 በመሆኑም አምላክ ሕዝቡ በቀይ ባሕር አቅራቢያ ባለው ምድረ በዳ በኩል ዞሮ እንዲሄድ አደረገ።+ እስራኤላውያንም ከግብፅ ምድር የወጡት የጦርነት አሰላለፍ ተከትለው ነበር።
-
-
ዘፀአት 15:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራ ይዟቸው ወጣ፤ እነሱም ወደ ሹር ምድረ በዳ ሄዱ፤ በምድረ በዳውም ለሦስት ቀን ያህል ተጓዙ፤ ሆኖም ውኃ አላገኙም ነበር።
-