ዘፍጥረት 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ 2 ሳሙኤል 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ 2 ሳሙኤል 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል።+ ጥፋት በሚያጠፋበት ጊዜም በሰዎች በትር፣ በሰው* ልጆች አለንጋ እቀጣዋለሁ።+