-
ኤርምያስ 32:17-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 “አቤቱ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ! እነሆ፣ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ሠርተሃል።+ አንተ ምንም የሚሳንህ ነገር የለም፤ 18 ለሺዎች ታማኝ ፍቅር ታሳያለህ፤ ይሁንና የአባቶችን በደል ከእነሱ በኋላ በሚመጡት ልጆቻቸው ላይ* ትመልሳለህ፤+ አንተ እውነተኛ፣ ታላቅና ኃያል አምላክ ነህ፤ ስምህም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው። 19 በምክር ታላቅ፣* በሥራም ኃያል ነህ፤+ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ለመክፈል+ ዓይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ።+
-