ሕዝቅኤል 34:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በእነሱ ላይ አንድ እረኛ ይኸውም አገልጋዬን ዳዊትን* አስነሳለሁ፤+ እሱም ይመግባቸዋል። እሱ ራሱ ያሰማራቸዋል፤ እረኛቸውም ይሆናል።+ ሕዝቅኤል 37:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 “‘“አገልጋዬ ዳዊት ንጉሣቸው ይሆናል፤+ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል።+ ድንጋጌዎቼን አክብረው ይመላለሳሉ፤ ደንቦቼንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።+