ዘዳግም 32:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 በቀልም ሆነ ቅጣት የእኔ ነው፤+አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ እግራቸው ይከዳቸዋል፤+የሚጠፉበት ቀን ቀርቧልና፤የሚጠብቃቸውም ነገር በፍጥነት ይመጣል።’ ዘዳግም 32:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 የሚያብረቀርቅ ሰይፌን ከሳልኩናእጄን ለፍርድ ካዘጋጀሁ፣+ተቃዋሚዎቼን እበቀላለሁ፤+የሚጠሉኝንም እቀጣለሁ። ኢሳይያስ 59:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ላደረጉት ነገር ብድራት ይከፍላቸዋል፦+ ቁጣን ለባላጋራዎቹ፣ በቀልን ለጠላቶቹ ይከፍላል።+ ለደሴቶችም የሚገባቸውን ዋጋ ይከፍላቸዋል።