ዘዳግም 33:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሲና መጣ፤+ከሴይርም ሆኖ አበራባቸው። ከፋራን ተራራማ አካባቢዎችም በክብር አበራ፤+ከእሱም ጋር አእላፋት ቅዱሳን* ነበሩ፤+በቀኙም ተዋጊዎቹ አሉ።+ መሳፍንት 5:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከሴይር+ በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ክልል እየገሰገስክ በመጣህ ጊዜ፣ምድር ተናወጠች፤ ሰማያትም ውኃ አወረዱ፤ደመናትም ውኃ አንዠቀዠቁ። መዝሙር 68:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አምላክ ሆይ፣ ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፣*+በረሃውንም አቋርጠህ በተጓዝክ ጊዜ (ሴላ) 8 ምድር ተናወጠች፤+በአምላክ ፊት ሰማይ ዝናብ አወረደ፤*ይህ የሲና ተራራ በአምላክ ይኸውም በእስራኤል አምላክ ፊት ተናወጠ።+
2 እንዲህ አለ፦ “ይሖዋ ከሲና መጣ፤+ከሴይርም ሆኖ አበራባቸው። ከፋራን ተራራማ አካባቢዎችም በክብር አበራ፤+ከእሱም ጋር አእላፋት ቅዱሳን* ነበሩ፤+በቀኙም ተዋጊዎቹ አሉ።+
7 አምላክ ሆይ፣ ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፣*+በረሃውንም አቋርጠህ በተጓዝክ ጊዜ (ሴላ) 8 ምድር ተናወጠች፤+በአምላክ ፊት ሰማይ ዝናብ አወረደ፤*ይህ የሲና ተራራ በአምላክ ይኸውም በእስራኤል አምላክ ፊት ተናወጠ።+