2 ዜና መዋዕል 36:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር። ኤርምያስ 11:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ “ድምፄን ስሙ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ* አጥብቄ ሳሳስባቸው ነበርና።+ 8 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዳቸው ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን ተከተሉ።+ ስለዚህ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ያዘዝኳቸውንና እነሱ ሥራ ላይ ያላዋሉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ በእነሱ ላይ አመጣሁባቸው።’”
15 የአባቶቻቸው አምላክ ይሖዋ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስፍራ ስለራራ መልእክተኞቹን እየላከ በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃቸው ነበር። 16 እነሱ ግን የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነድና+ ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ በእውነተኛው አምላክ መልእክተኞች ላይ ያላግጡ፣+ ቃሉን ይንቁና+ በነቢያቱ ላይ ያፌዙ+ ነበር።
7 አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ “ድምፄን ስሙ” በማለት ደግሜ ደጋግሜ* አጥብቄ ሳሳስባቸው ነበርና።+ 8 እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዳቸው ግትር ሆነው የገዛ ክፉ ልባቸውን ተከተሉ።+ ስለዚህ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ያዘዝኳቸውንና እነሱ ሥራ ላይ ያላዋሉትን የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ሁሉ በእነሱ ላይ አመጣሁባቸው።’”