ዕዝራ 6:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 የአይሁዳውያን ሽማግሌዎችም ነቢዩ ሐጌና+ የኢዶ የልጅ ልጅ ዘካርያስ+ በተናገሩት ትንቢት ተበረታተው ግንባታውን ማከናወናቸውንና ሥራውን ማፋጠናቸውን ቀጠሉ፤+ በእስራኤል አምላክ ትእዛዝ መሠረት+ እንዲሁም በቂሮስ፣+ በዳርዮስና+ በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ+ ትእዛዝ መሠረት ቤቱን ገንብተው አጠናቀቁ። ዘካርያስ 1:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 1 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣+ በስምንተኛው ወር የይሖዋ ቃል ወደ ኢዶ ልጅ፣ ወደ ቤራክያህ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ*+ እንዲህ ሲል መጣ፦
14 የአይሁዳውያን ሽማግሌዎችም ነቢዩ ሐጌና+ የኢዶ የልጅ ልጅ ዘካርያስ+ በተናገሩት ትንቢት ተበረታተው ግንባታውን ማከናወናቸውንና ሥራውን ማፋጠናቸውን ቀጠሉ፤+ በእስራኤል አምላክ ትእዛዝ መሠረት+ እንዲሁም በቂሮስ፣+ በዳርዮስና+ በፋርሱ ንጉሥ በአርጤክስስ+ ትእዛዝ መሠረት ቤቱን ገንብተው አጠናቀቁ።