ዘፍጥረት 2:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 በዚህም ምክንያት ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል።* ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።+ ማቴዎስ 5:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ምንዝር ለመፈጸም እንድትጋለጥ ያደርጋታል፤ እንዲሁም በዚህ መንገድ የተፈታችን ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+ ማቴዎስ 19:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ማርቆስ 10:5-9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ ይህን ትእዛዝ የጻፈላችሁ ልባችሁ ደንዳና+ መሆኑን አይቶ ነው።+ 6 ይሁን እንጂ በፍጥረት መጀመሪያ ‘አምላክ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ 7 ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤+ 8 ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’፤+ በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። 9 ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን* ማንም ሰው አይለያየው።”+
32 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ምንዝር ለመፈጸም እንድትጋለጥ ያደርጋታል፤ እንዲሁም በዚህ መንገድ የተፈታችን ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+
5 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴ ይህን ትእዛዝ የጻፈላችሁ ልባችሁ ደንዳና+ መሆኑን አይቶ ነው።+ 6 ይሁን እንጂ በፍጥረት መጀመሪያ ‘አምላክ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።+ 7 ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤+ 8 ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’፤+ በመሆኑም ከዚህ በኋላ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። 9 ስለዚህ አምላክ ያጣመረውን* ማንም ሰው አይለያየው።”+