ኢሳይያስ 42:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 አይጮኽም ወይም ድምፁን ከፍ አያደርግም፤ድምፁንም በጎዳና ላይ አያሰማም።+ ማቴዎስ 12:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ኢየሱስም ይህን ሲያውቅ አካባቢውን ለቆ ሄደ። ብዙ ሰዎችም ተከትለውት ሄዱ፤+ እሱም የታመሙትን ሁሉ ፈወሳቸው፤ 16 ሆኖም የእሱን ማንነት ለሌሎች እንዳይገልጹ በጥብቅ አዘዛቸው፤+ ማርቆስ 1:44, 45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 እንዲህም አለው፦ “ለማንም አንዳች ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ያዘዛቸውንም ነገሮች አቅርብ፤+ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ።”+ 45 ሰውየው ግን ከሄደ በኋላ የሆነውን ነገር በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም በየቦታው አሰራጨ፤ ስለሆነም ኢየሱስ ከዚህ በኋላ በግልጽ ወደ ከተማ መግባት ባለመቻሉ ከከተማ ውጭ ገለል ባሉ ቦታዎች ይኖር ጀመር። ይሁንና ሰዎች ከየአቅጣጫው ወደ እሱ መምጣታቸውን ቀጠሉ።+ ማርቆስ 7:35, 36 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 በዚህ ጊዜ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤+ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ። 36 ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤+ እነሱ ግን ይበልጥ ባስጠነቀቃቸው መጠን የዚያኑ ያህል ነገሩን በስፋት ያወሩ ነበር።+
15 ኢየሱስም ይህን ሲያውቅ አካባቢውን ለቆ ሄደ። ብዙ ሰዎችም ተከትለውት ሄዱ፤+ እሱም የታመሙትን ሁሉ ፈወሳቸው፤ 16 ሆኖም የእሱን ማንነት ለሌሎች እንዳይገልጹ በጥብቅ አዘዛቸው፤+
44 እንዲህም አለው፦ “ለማንም አንዳች ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ሙሴ ያዘዛቸውንም ነገሮች አቅርብ፤+ ካህናቱም ማስረጃውን ይመለከታሉ።”+ 45 ሰውየው ግን ከሄደ በኋላ የሆነውን ነገር በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም በየቦታው አሰራጨ፤ ስለሆነም ኢየሱስ ከዚህ በኋላ በግልጽ ወደ ከተማ መግባት ባለመቻሉ ከከተማ ውጭ ገለል ባሉ ቦታዎች ይኖር ጀመር። ይሁንና ሰዎች ከየአቅጣጫው ወደ እሱ መምጣታቸውን ቀጠሉ።+
35 በዚህ ጊዜ ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤+ ምላሱም ተፈቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ። 36 ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤+ እነሱ ግን ይበልጥ ባስጠነቀቃቸው መጠን የዚያኑ ያህል ነገሩን በስፋት ያወሩ ነበር።+