-
ማርቆስ 4:30-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የአምላክን መንግሥት ከምን ጋር ልናነጻጽረው እንችላለን? ወይስ በምን ምሳሌ ልንገልጸው እንችላለን? 31 መሬት ላይ በተዘራች ጊዜ በምድር ላይ ካሉ ዘሮች ሁሉ እጅግ የምታንስን የሰናፍጭ ዘር ይመስላል።+ 32 ከተዘራች በኋላ ግን አድጋ ከሌሎች ተክሎች ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ ትላልቅ ቅርንጫፎችም ታወጣለች፤ በመሆኑም የሰማይ ወፎች በጥላዋ ሥር መስፈሪያ ያገኛሉ።”
-
-
ሉቃስ 13:18, 19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የአምላክ መንግሥት ከምን ጋር ይመሳሰላል? ከምንስ ጋር ላነጻጽረው? 19 አንድ ሰው ወስዶ በአትክልት ቦታው ከዘራት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤ ይህች ዘር አድጋ ዛፍ ሆነች፤ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎቿ ላይ ሰፈሩ።”+
-