-
ማቴዎስ 13:31, 32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 ደግሞም እንዲህ ሲል ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፦ “መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው ወስዶ እርሻው ውስጥ ከተከላት አንዲት የሰናፍጭ ዘር ጋር ይመሳሰላል፤+ 32 የሰናፍጭ ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ያነሰች ብትሆንም ስታድግ ግን ከተክሎች ሁሉ በልጣ ዛፍ ስለምትሆን የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቿ ላይ መስፈሪያ ያገኛሉ።”
-
-
ማርቆስ 4:30-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ደግሞም እንዲህ አለ፦ “የአምላክን መንግሥት ከምን ጋር ልናነጻጽረው እንችላለን? ወይስ በምን ምሳሌ ልንገልጸው እንችላለን? 31 መሬት ላይ በተዘራች ጊዜ በምድር ላይ ካሉ ዘሮች ሁሉ እጅግ የምታንስን የሰናፍጭ ዘር ይመስላል።+ 32 ከተዘራች በኋላ ግን አድጋ ከሌሎች ተክሎች ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች፤ ትላልቅ ቅርንጫፎችም ታወጣለች፤ በመሆኑም የሰማይ ወፎች በጥላዋ ሥር መስፈሪያ ያገኛሉ።”
-