53 ወደ የብስ በተሻገሩ ጊዜ ጌንሴሬጥ ደረሱ፤ በአቅራቢያውም ጀልባዋን አቆሙ።+ 54 ሆኖም ከጀልባዋ እንደወረዱ ሰዎች አወቁት። 55 ወደ አካባቢው ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በቃሬዛ እየተሸከሙ እሱ ይገኝበታል ወደተባለው ቦታ ያመጡ ጀመር። 56 በገባበት መንደር ወይም ከተማ ወይም ገጠር ሁሉ ሕመምተኞቹን በገበያ ስፍራ ያስቀምጡ ነበር፤ የልብሱንም ዘርፍ እንኳ ለመንካት ይማጸኑት ነበር።+ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።