-
ማቴዎስ 21:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ እኔ በበለስ ዛፏ ላይ ያደረግኩትን ማድረግ ብቻ ሳይሆን ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት እንኳ ይሆንላችኋል።+
-
-
ማርቆስ 11:23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና በልቡ ሳይጠራጠር የተናገረው ነገር እንደሚፈጸም ቢያምን ይሆንለታል።+
-
-
ሉቃስ 17:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰናፍጭ ዘር የሚያህል እምነት ካላችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕሩ ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዛችኋል።+
-