-
ማቴዎስ 17:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 እሱም “እምነታችሁ ስላነሰ ነው። እውነት እላችኋለሁ፣ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል እምነት ካላችሁ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደዚያ ሂድ’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ነገር አይኖርም”+ አላቸው።
-
-
ማርቆስ 11:22, 23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “በአምላክ ላይ እምነት ይኑራችሁ። 23 እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነስተህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና በልቡ ሳይጠራጠር የተናገረው ነገር እንደሚፈጸም ቢያምን ይሆንለታል።+
-
-
ሉቃስ 17:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ጌታም እንዲህ አለ፦ “የሰናፍጭ ዘር የሚያህል እምነት ካላችሁ ይህን የሾላ ዛፍ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕሩ ውስጥ ተተከል!’ ብትሉት ይታዘዛችኋል።+
-