ዳንኤል 9:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 “እሱም ለብዙዎች ቃል ኪዳኑን ለአንድ ሳምንት ያጸናል፤ በሳምንቱም አጋማሽ ላይ መሥዋዕትንና የስጦታ መባን ያስቀራል።+ “ጥፋት የሚያመጣውም በአስጸያፊ ነገሮች ክንፍ ላይ ሆኖ ይመጣል፤+ ጥፋት እስኪመጣም ድረስ የተወሰነው ነገር በወደመው ነገር ላይ ይፈስሳል።” ዳንኤል 11:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከእሱ የሚወጡ ክንዶች ይቆማሉ፤* እነሱም ምሽጉን ይኸውም መቅደሱን ያረክሳሉ፤+ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ።+ “ጥፋት የሚያመጣውንም ርኩስ ነገር በዚያ ያኖራሉ።+ ዳንኤል 12:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “የዘወትሩ መሥዋዕት+ ከተቋረጠበትና ጥፋት የሚያመጣው ርኩስ ነገር ከቆመበት+ ጊዜ አንስቶ 1,290 ቀን ይሆናል። ማርቆስ 13:14-18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “ይሁንና ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’+ በማይገባው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል፤ በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።+ 15 በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው አይውረድ፤ አንዳችም ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አይግባ፤ 16 በእርሻም ያለ መደረቢያውን ለመውሰድ ወደ ኋላ አይመለስ። 17 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ 18 ይህ በክረምት እንዳይሆን ዘወትር ጸልዩ፤ ሉቃስ 21:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 “ይሁንና ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ+ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ።+
27 “እሱም ለብዙዎች ቃል ኪዳኑን ለአንድ ሳምንት ያጸናል፤ በሳምንቱም አጋማሽ ላይ መሥዋዕትንና የስጦታ መባን ያስቀራል።+ “ጥፋት የሚያመጣውም በአስጸያፊ ነገሮች ክንፍ ላይ ሆኖ ይመጣል፤+ ጥፋት እስኪመጣም ድረስ የተወሰነው ነገር በወደመው ነገር ላይ ይፈስሳል።”
31 ከእሱ የሚወጡ ክንዶች ይቆማሉ፤* እነሱም ምሽጉን ይኸውም መቅደሱን ያረክሳሉ፤+ የዘወትሩንም መሥዋዕት ያስቀራሉ።+ “ጥፋት የሚያመጣውንም ርኩስ ነገር በዚያ ያኖራሉ።+
14 “ይሁንና ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’+ በማይገባው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል፤ በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።+ 15 በጣሪያ* ላይ ያለ ሰው አይውረድ፤ አንዳችም ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አይግባ፤ 16 በእርሻም ያለ መደረቢያውን ለመውሰድ ወደ ኋላ አይመለስ። 17 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ 18 ይህ በክረምት እንዳይሆን ዘወትር ጸልዩ፤