ሉቃስ 22:21-23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ ከእኔ ጋር በማዕድ ነው።+ 22 እርግጥ የሰው ልጅ አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት ይሄዳል፤+ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!”+ 23 ስለዚህ ከመካከላቸው በእርግጥ ይህን የሚያደርገው ማን ሊሆን እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር።+ ዮሐንስ 6:70 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 70 ኢየሱስም መልሶ “አሥራ ሁለታችሁንም የመረጥኳችሁ እኔ አይደለሁም?+ ይሁንና ከመካከላችሁ አንዱ ስም አጥፊ* ነው” አላቸው።+ ዮሐንስ 13:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ መንፈሱ ተረብሾ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል”+ ሲል በግልጽ ተናገረ። 22 ደቀ መዛሙርቱም ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ግራ ገብቷቸው እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀመር።+
21 “ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ ከእኔ ጋር በማዕድ ነው።+ 22 እርግጥ የሰው ልጅ አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት ይሄዳል፤+ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት!”+ 23 ስለዚህ ከመካከላቸው በእርግጥ ይህን የሚያደርገው ማን ሊሆን እንደሚችል እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር።+
21 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ መንፈሱ ተረብሾ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል”+ ሲል በግልጽ ተናገረ። 22 ደቀ መዛሙርቱም ስለ ማን እየተናገረ እንዳለ ግራ ገብቷቸው እርስ በርሳቸው ይተያዩ ጀመር።+