67 “አንተ ክርስቶስ ከሆንክ ንገረን።”+ እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “ብነግራችሁም እንኳ ፈጽሞ አታምኑም። 68 ብጠይቃችሁም አትመልሱም። 69 ያም ሆነ ይህ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ+ በኃያሉ አምላክ ቀኝ ይቀመጣል።”+ 70 በዚህ ጊዜ ሁሉም “ስለዚህ የአምላክ ልጅ ነህ ማለት ነው?” አሉት። እሱም “የአምላክ ልጅ መሆኔን እናንተው ራሳችሁ እየተናገራችሁ ነው” አላቸው። 71 እነሱም “ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ ያስፈልገናል? እኛ ራሳችን ከገዛ አፉ ሰምተነዋል” አሉ።+