-
ማርቆስ 15:29-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 በዚያ የሚያልፉም ይሰድቡትና ራሳቸውን እየነቀነቁ+ እንዲህ ይሉት ነበር፦ “ቤተ መቅደሱን አፍርሼ በሦስት ቀን እሠራዋለሁ ባይ!+ 30 እስቲ ከተሰቀልክበት እንጨት* ላይ ወርደህ ራስህን አድን።” 31 የካህናት አለቆችም እንደዚሁ ከጸሐፍት ጋር ሆነው እርስ በርሳቸው እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ነበር፦ “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም!+ 32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ እስቲ አሁን ከተሰቀለበት እንጨት* ይውረድ።”+ ከእሱ ጋር በእንጨት ላይ የተሰቀሉትም እንኳ ሳይቀሩ ይነቅፉት ነበር።+
-