17 ወደ ኢየሩሳሌም እየወጡ ሳሉ ኢየሱስ 12ቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ነጥሎ ወሰዳቸው፤ በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ አላቸው፦+ 18 “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እየወጣን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለጸሐፍት አልፎ ይሰጣል። እነሱም ሞት ይፈርዱበታል፤+ 19 እንዲሁም እንዲያፌዙበት፣ እንዲገርፉትና በእንጨት ላይ እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤+ እሱም በሦስተኛው ቀን ይነሳል።”+