-
ማቴዎስ 21:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረቡና በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወደምትገኘው ወደ ቤተፋጌ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤+ 2 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ እዚያ እንደደረሳችሁም አንዲት የታሰረች አህያ ከነውርንጭላዋ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው። 3 ማንም ሰው ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ይልካቸዋል።”
-
-
ሉቃስ 19:29-34አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ደብረ ዘይት በተባለው ተራራ+ ወደሚገኙት ወደ ቤተፋጌ እና ወደ ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው፤+ 30 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደሩ ከገባችሁም በኋላ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጭላ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደዚህ አምጡት። 31 ይሁን እንጂ ማንም ሰው ‘የምትፈቱት ለምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልገዋል’ ብላችሁ ንገሩት።” 32 የተላኩትም ሄደው ልክ እንዳላቸው ሆኖ አገኙት።+ 33 ውርንጭላውን እየፈቱ ሳሉ ግን ባለቤቶቹ “ውርንጭላውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። 34 እነሱም “ጌታ ይፈልገዋል” አሉ።
-