-
ማቴዎስ 21:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 ወደ ኢየሩሳሌም በተቃረቡና በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወደምትገኘው ወደ ቤተፋጌ በደረሱ ጊዜ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤+ 2 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ እዚያ እንደደረሳችሁም አንዲት የታሰረች አህያ ከነውርንጭላዋ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው። 3 ማንም ሰው ቢጠይቃችሁ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ይልካቸዋል።”
-
-
ማርቆስ 11:1-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ወደ ኢየሩሳሌም፣ በደብረ ዘይት ተራራ ወዳሉት ወደ ቤተፋጌ እና ወደ ቢታንያ+ በተቃረቡ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሁለቱን ላካቸው፤+ 2 እንዲህም አላቸው፦ “ወደዚያ ወደምታዩት መንደር ሂዱ፤ ወደ መንደሩም እንደገባችሁ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጭላ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፈታችሁ ወደዚህ አምጡት። 3 ማንም ሰው ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ ‘ጌታ ይፈልገዋል፤ ደግሞም ወዲያውኑ ወደዚህ ይመልሰዋል’ በሉት።” 4 እነሱም ሄዱ፤ ውርንጭላውንም በአንድ ጠባብ መንገድ ዳር፣ ደጃፍ ላይ ታስሮ አገኙት።+ 5 በዚያ ከቆሙት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ “ውርንጭላውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። 6 እነሱም ኢየሱስ ያለውን ነገሯቸው፤ ከዚያም ፈቀዱላቸው።
-