-
ማቴዎስ 26:6-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ኢየሱስ በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን+ ቤት ሳለ 7 አንዲት ሴት በጣም ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እሱ ቀረበች፤ እየበላ ሳለም ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር። 8 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ ተቆጥተው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሁሉ ብክነት ለምንድን ነው? 9 ይህ ዘይት እኮ በውድ ዋጋ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር።”
-
-
ዮሐንስ 12:2-5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 በዚያም የራት ግብዣ አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግላቸው የነበረ+ ሲሆን አልዓዛር ግን ከእሱ ጋር ከሚበሉት አንዱ ነበር። 3 ከዚያም ማርያም ግማሽ ሊትር ገደማ* የሚሆን እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ አምጥታ በኢየሱስ እግር ላይ አፈሰሰች፤ እግሩንም በፀጉሯ አብሳ አደረቀች። ቤቱም በዘይቱ መዓዛ ታወደ።+ 4 ሆኖም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነውና አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ+ እንዲህ አለ፦ 5 “ይህ ዘይት በ300 ዲናር* ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?”
-