-
ማርቆስ 14:3-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን ቤት እየበላ ሳለ አንዲት ሴት እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። ብልቃጡንም ሰብራ በመክፈት ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር።+ 4 በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ተቆጥተው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ዘይት እንዲህ የሚባክነው ለምንድን ነው? 5 ከ300 ዲናር* በላይ ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር!” በሴትየዋም እጅግ ተበሳጩ።* 6 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “ተዉአት። ለምን ታስቸግሯታላችሁ? እሷ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች።+ 7 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ በፈለጋችሁ ጊዜ ሁሉ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።+ 8 እሷ የምትችለውን አድርጋለች፤ ሰውነቴን ለቀብሬ ለማዘጋጀት ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት አስቀድማ ቀብታዋለች።+ 9 እውነት እላችኋለሁ፣ በመላው ዓለም ምሥራቹ በሚሰበክበት+ ቦታ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችውም መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”+
-
-
ዮሐንስ 12:1-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 የፋሲካ በዓል ከመድረሱ ከስድስት ቀን በፊት ኢየሱስ፣ ከሞት ያስነሳው አልዓዛር+ ወደሚኖርባት ወደ ቢታንያ መጣ። 2 በዚያም የራት ግብዣ አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግላቸው የነበረ+ ሲሆን አልዓዛር ግን ከእሱ ጋር ከሚበሉት አንዱ ነበር። 3 ከዚያም ማርያም ግማሽ ሊትር ገደማ* የሚሆን እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ አምጥታ በኢየሱስ እግር ላይ አፈሰሰች፤ እግሩንም በፀጉሯ አብሳ አደረቀች። ቤቱም በዘይቱ መዓዛ ታወደ።+ 4 ሆኖም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነውና አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ+ እንዲህ አለ፦ 5 “ይህ ዘይት በ300 ዲናር* ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” 6 እንዲህ ያለው ግን ለድሆች አስቦ ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ሣጥኑን ይይዝ የነበረው እሱ በመሆኑ ወደ ሣጥኑ ከሚገባው ገንዘብ የመስረቅ ልማድ ነበረው። 7 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ለቀብሬ ቀን ለማዘጋጀት+ ብላ ያደረገችው ስለሆነ ይህን ልማድ እንዳትፈጽም አትከልክሏት። 8 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤+ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።”+
-