-
ማቴዎስ 12:9-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚያ ስፍራ ከሄደ በኋላ ወደ ምኩራባቸው ገባ፤ 10 በዚያም እጁ የሰለለ* አንድ ሰው ነበር።+ እነሱም ኢየሱስን መክሰስ ፈልገው “በሰንበት መፈወስ በሕግ ተፈቅዷል?” ሲሉ ጠየቁት።+ 11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ያለው ሰው ቢኖርና በሰንበት ቀን ጉድጓድ ውስጥ ቢገባበት በጉን ጎትቶ የማያወጣው ይኖራል?+ 12 ታዲያ ሰው ከበግ እጅግ አይበልጥም? ስለዚህ በሰንበት መልካም ነገር ማድረግ ተፈቅዷል።” 13 ከዚያም ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እጁን ዘረጋ፤ እጁም እንደ ሌላኛው እጁ ደህና ሆነለት። 14 ፈሪሳውያኑ ግን ወጥተው እሱን ለመግደል አሴሩ።
-
-
ሉቃስ 6:6-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 በሌላ የሰንበት ቀን+ ወደ ምኩራብ ገብቶ ያስተምር ጀመር። በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ* አንድ ሰው ነበር።+ 7 ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም ኢየሱስን የሚከሱበት ምክንያት ማግኘት ይፈልጉ ስለነበር በሰንበት ይፈውስ እንደሆነ ለማየት በትኩረት ይከታተሉት ነበር። 8 እሱ ግን ሐሳባቸውን አውቆ+ ስለነበር እጁ የሰለለበትን* ሰው “ተነሳና መሃል ላይ ቁም” አለው። ሰውየውም ተነስቶ በዚያ ቆመ። 9 ከዚያም ኢየሱስ “እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ፤ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት* ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው።+ 10 በዙሪያው ያሉትን ሁሉ ከተመለከተ በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ” አለው። ሰውየውም እንደተባለው አደረገ፤ እጁም ዳነለት። 11 እነሱ ግን እጅግ ተቆጡ፤ በኢየሱስ ላይ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉም እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ጀመር።
-