የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 8:24-27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 እነሆ፣ በጉዞ ላይ ሳሉ በባሕሩ ላይ ኃይለኛ ማዕበል ስለተነሳ ጀልባዋ በውኃ ተሞልታ ልትሰጥም ተቃረበች፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።+ 25 እነሱም ወደ እሱ ቀርበው ቀሰቀሱትና “ጌታ ሆይ፣ ማለቃችን እኮ ነው፤ አድነን!” አሉት። 26 እሱ ግን “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትሸበራላችሁ?”* አላቸው።+ ከዚያም ተነስቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሰፈነ።+ 27 ሰዎቹም ተደንቀው “ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? ነፋስና ባሕር እንኳ ይታዘዙለታል” አሉ።

  • ማርቆስ 4:37-41
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 37 በዚህ ጊዜ እጅግ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተነሳ፤ ማዕበሉም ከጀልባዋ ጋር እየተላተመ ወደ ውስጥ ይገባ ጀመር፤ ከዚህም የተነሳ ጀልባዋ በውኃ ልትሞላ ተቃረበች።+ 38 ኢየሱስ ግን በጀልባዋ የኋለኛ ክፍል ትራስ* ተንተርሶ ተኝቶ ነበር። ስለዚህ ቀስቅሰውት “መምህር፣ ስናልቅ ዝም ብለህ ታያለህ?” አሉት። 39 በዚህ ጊዜ ተነስቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል! ረጭ በል!” አለው።+ ነፋሱ ቆመ፤ ታላቅ ጸጥታም ሰፈነ። 40 ከዚያም “ለምን ትሸበራላችሁ?* አሁንም እምነት የላችሁም?” አላቸው። 41 እነሱ ግን በታላቅ ፍርሃት ተውጠው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ባሕር እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ