ማቴዎስ 16:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያገኛታል።+ ማርቆስ 8:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ሕይወቱን* ማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታልና፤ ለእኔና ለምሥራቹ ሲል ሕይወቱን* የሚያጣ ሁሉ ግን ያድናታል።+ ዮሐንስ 12:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሕይወቱን የሚወድ ሁሉ* ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን* የሚጠላ+ ሁሉ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።+ የሐዋርያት ሥራ 20:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ይሁንና ሩጫዬን እስካጠናቀቅኩ+ እንዲሁም ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ በመመሥከር* ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እስከፈጸምኩ ድረስ ሕይወቴ* ምንም አያሳሳኝም።* ራእይ 2:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ።+ እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ እንድትፈተኑና ለአሥር ቀን መከራ እንድትቀበሉ ዲያብሎስ አንዳንዶቻችሁን እስር ቤት ይከታል። እስከ ሞት ድረስ ታማኝነትህን አስመሥክር፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።+
24 ይሁንና ሩጫዬን እስካጠናቀቅኩ+ እንዲሁም ስለ አምላክ ጸጋ የሚገልጸውን ምሥራች በተሟላ ሁኔታ በመመሥከር* ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልኩትን አገልግሎት እስከፈጸምኩ ድረስ ሕይወቴ* ምንም አያሳሳኝም።*
10 ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ።+ እነሆ፣ ሙሉ በሙሉ እንድትፈተኑና ለአሥር ቀን መከራ እንድትቀበሉ ዲያብሎስ አንዳንዶቻችሁን እስር ቤት ይከታል። እስከ ሞት ድረስ ታማኝነትህን አስመሥክር፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።+