-
ማቴዎስ 12:38-42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 ከዚያም ከጸሐፍትና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ “መምህር፣ ምልክት እንድታሳየን እንፈልጋለን” አሉት።+ 39 እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ “ክፉና አመንዝራ* ትውልድ ሁልጊዜ ምልክት ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከነቢዩ ዮናስ ምልክት በስተቀር ምንም ምልክት አይሰጠውም።+ 40 ዮናስ በትልቅ ዓሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበረ+ ሁሉ የሰው ልጅም በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቆያል።+ 41 የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል። ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።+ 42 የደቡብ ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች+ በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትኮንነዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+
-