-
ፊልጵስዩስ 3:12-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 አሁን ሽልማቱን አግኝቻለሁ ወይም አሁን ወደ ፍጽምና ደርሻለሁ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ እኔን የመረጠበትን ያን ነገር የራሴ ማድረግ እችል እንደሆነ ለማየት ጥረት እያደረግኩ ነው።+ 13 ወንድሞች፣ እኔ እንዳገኘሁት አድርጌ አላስብም፤ ነገር ግን ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ፦ ከኋላዬ ያሉትን ነገሮች እየረሳሁ+ ከፊቴ ወዳሉት ነገሮች እንጠራራለሁ፤+ 14 አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚሰጠውን የሰማያዊውን ሕይወት+ ሽልማት አገኝ ዘንድ ግቡ ላይ ለመድረስ እየተጣጣርኩ ነው።+
-
-
1 ጢሞቴዎስ 6:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ የተጠራህለትንና በብዙ ምሥክሮች ፊት በጥሩ ሁኔታ በይፋ የተናገርክለትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ።
-