-
ማቴዎስ 27:22-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 ጲላጦስም “እንግዲያው ክርስቶስ የሚባለውን ኢየሱስን ምን ባደርገው ይሻላል?” አላቸው። ሁሉም “ይሰቀል!”* አሉ።+ 23 እሱም “ለምን? ምን ያጠፋው ነገር አለ?” አላቸው። እነሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ የባሰ መጮኻቸውን ቀጠሉ።+
24 ጲላጦስ ያደረገው ጥረት ምንም የፈየደው ነገር እንደሌለ ከዚህ ይልቅ ሁከት እያስነሳ መሆኑን በመገንዘብ “ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ። ከዚህ በኋላ ተጠያቂ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ” በማለት ውኃ አምጥቶ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ። 25 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።+ 26 ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ+ በእንጨት ላይ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።+
-
-
ዮሐንስ 19:12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 ከዚህ የተነሳ ጲላጦስ ኢየሱስን መፍታት የሚችልበትን መንገድ ያስብ ጀመር፤ አይሁዳውያኑ ግን “ይህን ሰው ከፈታኸው አንተ የቄሳር ወዳጅ አይደለህም። ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሰው ሁሉ የቄሳር ተቃዋሚ ነው” እያሉ ጮኹ።+
-