የሐዋርያት ሥራ 6:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የተናገሩት ነገር ሁሉንም ደስ አሰኛቸው፤ ስለሆነም ጠንካራ እምነት የነበረውንና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን እንዲሁም ፊልጶስን፣+ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞንን፣ ፓርሜናስንና ወደ ይሁዲነት ተለውጦ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። 6 ሐዋርያትም ፊት አቀረቧቸው፤ እነሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።+ የሐዋርያት ሥራ 19:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ጳውሎስም እጁን በላያቸው በጫነ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤+ እነሱም በባዕድ ቋንቋዎች መናገርና መተንበይ ጀመሩ።+ 2 ጢሞቴዎስ 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ስለዚህ በአንተ ላይ እጄን በጫንኩበት+ ጊዜ የተቀበልከውን የአምላክ ስጦታ በቅንዓት እንድትጠቀምበት* አሳስብሃለሁ።
5 የተናገሩት ነገር ሁሉንም ደስ አሰኛቸው፤ ስለሆነም ጠንካራ እምነት የነበረውንና በመንፈስ ቅዱስ የተሞላውን እስጢፋኖስን እንዲሁም ፊልጶስን፣+ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞንን፣ ፓርሜናስንና ወደ ይሁዲነት ተለውጦ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። 6 ሐዋርያትም ፊት አቀረቧቸው፤ እነሱም ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።+