የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሐዋርያት ሥራ 20:22, 23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 22 አሁን ደግሞ እዚያ ምን እንደሚደርስብኝ ባላውቅም መንፈስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው፤ 23 እርግጥ ነው፣ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ በደረስኩበት ከተማ ሁሉ በተደጋጋሚ ያሳስበኛል።+

  • የሐዋርያት ሥራ 21:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ወደ እኛም መጥቶ የጳውሎስን ቀበቶ በመውሰድ የራሱን እግርና እጅ ካሰረ በኋላ እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ‘አይሁዳውያን የዚህን ቀበቶ ባለቤት በኢየሩሳሌም እንዲህ አድርገው ያስሩታል፤+ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።’”+

  • 2 ቆሮንቶስ 11:23-28
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 23 የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸው? እንደ እብድ ሰው ልናገርና እኔ ከሁሉ በላቀ ደረጃ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፦ ከሁሉም ይበልጥ ሠርቻለሁ፣+ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፣+ ብዙ ጊዜ ተደብድቤአለሁ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ሞት አፋፍ ደርሻለሁ።+ 24 አይሁዳውያን ለ40 ጅራፍ አንድ የቀረው ግርፋት አምስት ጊዜ ገርፈውኛል፤+ 25 ሦስት ጊዜ በዱላ ተደብድቤአለሁ፤+ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወግሬአለሁ፤+ ሦስት ጊዜ የመርከብ መሰበር አደጋ አጋጥሞኛል፤+ አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባሕር ላይ አሳልፌአለሁ፤ 26 ብዙ ጊዜ ተጉዣለሁ፤ ደግሞም በወንዝ ሙላት ለሚመጣ አደጋ፣ ዘራፊዎች ለሚያደርሱት አደጋ፣ የገዛ ወገኖቼ ለሚያደርሱት አደጋ፣+ ከአሕዛብ ለሚሰነዘር አደጋ፣+ በከተማ፣+ በምድረ በዳና በባሕር ላይ ለሚያጋጥም አደጋ እንዲሁም በሐሰተኛ ወንድሞች መካከል ለሚያጋጥም አደጋ ተጋልጬ ነበር፤ 27 ብዙ ጥሬአለሁ፤ ብዙ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ ሳልተኛ አድሬአለሁ፤+ ተርቤአለሁ፤ ተጠምቻለሁ፤+ ብዙ ጊዜ ምግብ በማጣት ተቸግሬአለሁ፤+ በብርድ ተቆራምጃለሁ፤ በልብስ እጦትም ተቸግሬአለሁ።

      28 ከእነዚህ ውጫዊ ችግሮች በተጨማሪ ዕለት ዕለት የሚያስጨንቀኝ* የጉባኤዎች ሁሉ ሐሳብ ነው።+

  • ቆላስይስ 1:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 ለእናንተ ስል በተቀበልኩት መከራ+ አሁን እየተደሰትኩ ነው፤ በክርስቶስ የተነሳ በአካሌ ላይ የሚደርሰው መከራ በዚህ ብቻ አያበቃም። ይህ መከራ እየደረሰብኝ ያለው ለአካሉ+ ይኸውም ለጉባኤው+ ስል ነው።

  • 2 ጢሞቴዎስ 1:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 አሁን መከራ እየተቀበልኩ ያለሁትም ለዚሁ ነው፤+ ሆኖም አላፍርበትም።+ ያመንኩበትን እሱን አውቀዋለሁና፤ በአደራ የሰጠሁትንም እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቆ ማቆየት እንደሚችል እተማመናለሁ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ