-
የሐዋርያት ሥራ 28:17-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 ይሁን እንጂ ከሦስት ቀን በኋላ የአይሁዳውያንን ታላላቅ ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። ሰዎቹም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “ወንድሞች፣ ምንም እንኳ ሕዝቡን ወይም የአባቶቻችንን ልማድ የሚጻረር ነገር ያልፈጸምኩ+ ቢሆንም በኢየሩሳሌም አስረው ለሮማውያን አሳልፈው ሰጥተውኛል።+ 18 እነሱም ከመረመሩኝ+ በኋላ ለሞት የሚያበቃ ምንም ጥፋት ስላላገኙብኝ ሊፈቱኝ ፈልገው ነበር።+ 19 ሆኖም አይሁዳውያን ይህን በተቃወሙ ጊዜ ለቄሳር ይግባኝ ለማለት ተገደድኩ፤+ ይህን ያደረግኩት ግን ሕዝቤን የምከስበት ነገር ኖሮኝ አይደለም።
-