-
1 ቆሮንቶስ 16:1አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ለቅዱሳን መዋጮ ማሰባሰብን በተመለከተ+ ደግሞ በገላትያ ለሚገኙ ጉባኤዎች የሰጠሁትን መመሪያ መከተል ትችላላችሁ።
-
-
2 ቆሮንቶስ 8:1-4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ወንድሞች፣ በመቄዶንያ+ ላሉት ጉባኤዎች ስለተሰጠው የአምላክ ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን። 2 ከባድ ፈተና ደርሶባቸው በመከራ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ታላቅ ደስታ የነበራቸው ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ* ልግስና አሳይተዋል፤ ይህን ያደረጉት በጣም ድሆች ሆነው ሳለ ነው። 3 እንደ አቅማቸው+ እንዲያውም ከአቅማቸው በላይ እንደሰጡ እመሠክርላቸዋለሁና፤+ 4 ምክንያቱም እነዚህ ወንድሞች ለቅዱሳን በልግስና በመስጠት፣ በእርዳታ አገልግሎቱ ለመካፈል መብት እንዲሰጣቸው በራሳቸው ፍላጎት ተነሳስተው ይለምኑን እንዲያውም ይማጸኑን ነበር።+
-
-
2 ቆሮንቶስ 9:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 እርዳታ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናችሁን አውቃለሁና፤ በመሆኑም “የአካይያ ወንድሞች ሌሎችን ለመርዳት ለአንድ ዓመት ያህል ዝግጁ ሆነው ሲጠባበቁ ቆይተዋል” ብዬ ለመቄዶንያ ወንድሞች በኩራት ተናግሬአለሁ፤ የእናንተ ቅንዓት ደግሞ አብዛኞቹን አነሳስቷል።
-