-
የሐዋርያት ሥራ 24:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 አገረ ገዢውም እንዲናገር በጭንቅላቱ ምልክት በሰጠው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፦
“ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ ሆነህ ስታገለግል መቆየትህን አውቃለሁ፤ በመሆኑም ስለ ራሴ የመከላከያ መልስ የማቀርበው በደስታ ነው።+
-
-
የሐዋርያት ሥራ 25:10-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፦ “እኔ ልዳኝበት በሚገባኝ በቄሳር የፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተ ራስህ በሚገባ እንደተገነዘብከው በአይሁዳውያን ላይ የፈጸምኩት ምንም በደል የለም። 11 በእርግጥ ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁና ለሞት የሚያበቃ ነገር ፈጽሜ ከሆነ+ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ ሰዎች ያቀረቡብኝ ክስ ሁሉ መሠረተ ቢስ ከሆነ ግን እነሱን ለማስደሰት ብሎ ማንም ሰው እኔን ለእነሱ አሳልፎ የመስጠት መብት የለውም። ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”+ 12 በዚህ ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ከተመካከረ በኋላ “ወደ ቄሳር ይግባኝ ስላልክ ወደ ቄሳር ትሄዳለህ” ሲል መለሰለት።
-