ዘፀአት 34:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው+ በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ”+ አለው። ዘዳግም 31:24-26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ+ እንደጨረሰ 25 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል። ዕብራውያን 7:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 እንግዲህ የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና ፍሬ ቢስ በመሆኑ ተሽሯል።+
24 ሙሴም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በመጽሐፍ ላይ ጽፎ+ እንደጨረሰ 25 የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት የሚሸከሙትን ሌዋውያኑን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ 26 “ይህን የሕግ መጽሐፍ+ ወስዳችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት+ አጠገብ አስቀምጡት፤ ይህም በዚያ በእናንተ ላይ ምሥክር ሆኖ ያገለግላል።