-
ማቴዎስ 27:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ኢየሱስም አገረ ገዢው ፊት ቀረበ፤ አገረ ገዢውም “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም መልሶ “አንተው ራስህ ተናገርከው” አለው።+
-
-
ዮሐንስ 18:33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
33 ስለሆነም ጲላጦስ ወደ ገዢው መኖሪያ ተመልሶ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “አንተ የአይሁዳውያን ንጉሥ ነህ?” አለው።+
-
-
ዮሐንስ 19:10, 11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ስለሆነም ጲላጦስ “መልስ አትሰጠኝም? ልፈታህም ሆነ ልገድልህ* ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም?” አለው። 11 ኢየሱስም “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን አይኖርህም ነበር። ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው የባሰ ኃጢአት ያለበት ለዚህ ነው” ሲል መለሰለት።
-