-
የሐዋርያት ሥራ 15:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ሰዎች መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ለመላክ በአንድ ልብ ወሰንን፤
-
-
የሐዋርያት ሥራ 15:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ስለዚህ ይህንኑ ነገር በቃልም እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል።+
-
-
ፊልጵስዩስ 2:19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
19 ስለ እናንተ በምሰማበት ጊዜ እንድበረታታ፣ ጌታ ኢየሱስ ቢፈቅድ ጢሞቴዎስን+ በቅርቡ ወደ እናንተ እንደምልከው ተስፋ አደርጋለሁ።
-
-
ቆላስይስ 4:7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 በጌታ ታማኝ አገልጋይና አብሮኝ ባሪያ የሆነው የተወደደው ወንድሜ ቲኪቆስ+ ስለ እኔ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል።
-
-
ቲቶ 1:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 አንተን በቀርጤስ የተውኩህ ያልተስተካከሉትን* ነገሮች እንድታስተካክልና በሰጠሁህ መመሪያ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፤
-