2 እነሱም ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ገዳይ መቅሰፍት የሚገባው ሁሉ በመቅሰፍት እንዲሞት ይሂድ፤
ሰይፍ የሚገባው ሁሉ በሰይፍ ይሙት፤+
ረሃብ የሚገባው ሁሉ በረሃብ ይሙት፤
በምርኮ መወሰድ የሚገባው ሁሉ ደግሞ ተማርኮ ይወሰድ!”’+
3 “‘እኔም አራት ዓይነት ጥፋት አዝባቸዋለሁ’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘እነሱም፦ ለመግደል ሰይፍ፣ ጎትቶ ለመውሰድ ውሾች እንዲሁም ለመሰልቀጥና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው።+