-
ዘፀአት 9:23-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 በመሆኑም ሙሴ በትሩን ወደ ሰማይ አነሳ፤ ይሖዋም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፤ እሳትም* በምድር ላይ ወረደ፤ ይሖዋ በግብፅ ምድር ላይ ያለማቋረጥ በረዶ እንዲወርድ አደረገ። 24 በረዶም ወረደ፤ በበረዶውም መካከል የእሳት ብልጭታ ነበር። በረዶውም እጅግ ከባድ ነበር፤ ግብፅ እንደ አገር ሆና ከተመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ በዚያች ምድር ላይ እንዲህ ያለ በረዶ ተከስቶ አያውቅም።+ 25 በረዶው ከሰው አንስቶ እስከ እንስሳ ድረስ በግብፅ ምድር በመስክ ላይ የነበረውን ማንኛውንም ነገር መታ፤ ዕፀዋቱን ሁሉና በሜዳ ላይ ያለውን ዛፍ በሙሉ አወደመ።+
-
-
መዝሙር 97:5አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 ተራሮች በይሖዋ ፊት፣
በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።+
-