የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ቆሮንቶስ 4
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ቆሮንቶስ የመጽሐፉ ይዘት

      • “መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል” (1-5)

      • ክርስቲያን አገልጋዮች የሚያሳዩት ትሕትና (6-13)

        • “ከተጻፈው አትለፍ” (6)

        • ክርስቲያኖች እንደ ትርዒት ይታያሉ (9)

      • ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጆቹ ያስባል (14-21)

1 ቆሮንቶስ 4:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የበታቾችና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 13:11፤ ሮም 16:25, 26

1 ቆሮንቶስ 4:3

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ፍርድ ቤት።”

1 ቆሮንቶስ 4:4

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ምሳሌ 21:2፤ ሮም 14:10፤ ዕብ 4:13

1 ቆሮንቶስ 4:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 7:1
  • +ምሳሌ 10:9፤ 2ቆሮ 10:18፤ 1ጢሞ 5:24, 25

1 ቆሮንቶስ 4:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 12:3፤ 2ቆሮ 12:20፤ 3ዮሐ 9
  • +1ቆሮ 1:12

1 ቆሮንቶስ 4:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዮሐ 3:27

1 ቆሮንቶስ 4:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ራእይ 20:4, 6
  • +2ጢሞ 2:12፤ ራእይ 3:21

1 ቆሮንቶስ 4:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሮም 8:36፤ 1ቆሮ 15:32፤ 2ቆሮ 6:4, 9
  • +ዕብ 10:33

1 ቆሮንቶስ 4:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 3:18

1 ቆሮንቶስ 4:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “በቡጢ እየተመታንና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ፊልጵ 4:12
  • +2ቆሮ 11:27
  • +ሥራ 14:19፤ 23:2፤ 2ቆሮ 11:24

1 ቆሮንቶስ 4:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሥራ 18:3፤ 20:34፤ 1ተሰ 2:9
  • +ሮም 12:14፤ 1ጴጥ 3:9
  • +ማቴ 5:44

1 ቆሮንቶስ 4:13

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እንለማመጣለን።”

  • *

    ወይም “ቆሻሻና፤ ትርኪ ምርኪና።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ጴጥ 2:23

1 ቆሮንቶስ 4:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “አስተማሪዎች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ገላ 4:19፤ 1ተሰ 2:11

1 ቆሮንቶስ 4:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ቆሮ 11:1፤ ፊልጵ 3:17፤ 1ተሰ 1:6

1 ቆሮንቶስ 4:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “መንገዶች።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ጢሞ 1:13

1 ቆሮንቶስ 4:19

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።

1 ቆሮንቶስ 4:21

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ቆሮ 13:10

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ቆሮ. 4:1ማቴ 13:11፤ ሮም 16:25, 26
1 ቆሮ. 4:4ምሳሌ 21:2፤ ሮም 14:10፤ ዕብ 4:13
1 ቆሮ. 4:5ማቴ 7:1
1 ቆሮ. 4:5ምሳሌ 10:9፤ 2ቆሮ 10:18፤ 1ጢሞ 5:24, 25
1 ቆሮ. 4:6ሮም 12:3፤ 2ቆሮ 12:20፤ 3ዮሐ 9
1 ቆሮ. 4:61ቆሮ 1:12
1 ቆሮ. 4:7ዮሐ 3:27
1 ቆሮ. 4:8ራእይ 20:4, 6
1 ቆሮ. 4:82ጢሞ 2:12፤ ራእይ 3:21
1 ቆሮ. 4:9ሮም 8:36፤ 1ቆሮ 15:32፤ 2ቆሮ 6:4, 9
1 ቆሮ. 4:9ዕብ 10:33
1 ቆሮ. 4:101ቆሮ 3:18
1 ቆሮ. 4:11ፊልጵ 4:12
1 ቆሮ. 4:112ቆሮ 11:27
1 ቆሮ. 4:11ሥራ 14:19፤ 23:2፤ 2ቆሮ 11:24
1 ቆሮ. 4:12ሥራ 18:3፤ 20:34፤ 1ተሰ 2:9
1 ቆሮ. 4:12ሮም 12:14፤ 1ጴጥ 3:9
1 ቆሮ. 4:12ማቴ 5:44
1 ቆሮ. 4:131ጴጥ 2:23
1 ቆሮ. 4:15ገላ 4:19፤ 1ተሰ 2:11
1 ቆሮ. 4:161ቆሮ 11:1፤ ፊልጵ 3:17፤ 1ተሰ 1:6
1 ቆሮ. 4:172ጢሞ 1:13
1 ቆሮ. 4:212ቆሮ 13:10
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ቆሮንቶስ 4:1-21

ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ

4 እንግዲህ ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና* የአምላክ ቅዱስ ሚስጥር በአደራ የተሰጠን መጋቢዎች እንደሆን አድርጎ ሊቆጥረን ይገባል።+ 2 በዚህ ረገድ መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል። 3 በእናንተም ሆነ በሰዎች ሸንጎ* ብመረመር ለእኔ ምንም ትርጉም የለውም። እኔም እንኳ ራሴን አልመረምርም። 4 ምክንያቱም ሕሊናዬ በሁሉም ነገር ንጹሕ ነው። ሆኖም ይህ ጻድቅ መሆኔን ያረጋግጣል ማለት አይደለም፤ እኔን የሚመረምረኝ ይሖዋ* ነው።+ 5 ስለዚህ ጊዜው ከመድረሱ በፊት በምንም ነገር ላይ አትፍረዱ፤+ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጠብቁ። እሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ነገር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ እንዲሁም በልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ምስጋናውን ይቀበላል።+

6 እንግዲህ ወንድሞች፣ አንዱን ከሌላው በማስበለጥ እንዳትታበዩ፣+ ለእናንተው ጥቅም ራሴንና አጵሎስን+ ምሳሌ አድርጌ በማቅረብ እነዚህን ነገሮች የተናገርኩት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ደንብ እንድትማሩ ነው። 7 ለመሆኑ አንተን ከሌላው የተለየህ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው? ደግሞስ ያልተቀበልከው ምን ነገር አለ?+ ከተቀበልክ ደግሞ እንዳልተቀበልክ ሆነህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?

8 እንግዲህ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል ማለት ነዋ! ባለጠጎች ሆናችኋላ! ያለእኛ ነግሣችኋል+ ማለት ነዋ! እኛም ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል ነገሥታት ሆናችሁ መግዛት ጀምራችሁ ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር!+ 9 አምላክ እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደተፈረደባቸው+ ሰዎች መጨረሻ ላይ ወደ መድረክ እንድንወጣ ያደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም፣ ለመላእክትና ለሰዎች ትርዒት ሆነናል።+ 10 እኛ በክርስቶስ የተነሳ ሞኞች ነን፤+ እናንተ ግን በክርስቶስ የተነሳ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ጠንካሮች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን ተዋርደናል። 11 እስከዚህ ሰዓት ድረስ እየተራብንና+ እየተጠማን፣+ እየተራቆትን፣ እየተደበደብንና*+ ቤት አጥተን እየተንከራተትን እንገኛለን፤ 12 እንዲሁም በገዛ እጃችን እየሠራን እንለፋለን።+ ሲሰድቡን እንባርካለን፤+ ስደት ሲያደርሱብን በትዕግሥት እናሳልፋለን፤+ 13 ስማችንን ሲያጠፉ በለዘበ አንደበት እንመልሳለን፤*+ እስካሁን ድረስ የዓለም ጉድፍና* የሁሉ ነገር ጥራጊ እንደሆንን ተደርገን እንታያለን።

14 እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ላሳፍራችሁ ብዬ ሳይሆን እንደተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ ነው። 15 ምንም እንኳ በክርስቶስ 10,000 ሞግዚቶች* ሊኖሯችሁ ቢችልም ብዙ አባቶች እንደሌሏችሁ ግን የተረጋገጠ ነው፤ በምሥራቹ አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ እኔ አባታችሁ ሆኛለሁና።+ 16 ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።+ 17 በጌታ ልጄ የሆነውን የምወደውንና ታማኝ የሆነውን ጢሞቴዎስን የምልክላችሁ ለዚህ ነው። እሱም በየስፍራው በሚገኙ ጉባኤዎች ሁሉ ሳስተምር የምጠቀምባቸውን ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቴን የማከናውንባቸውን ዘዴዎች* ያሳስባችኋል።+

18 አንዳንዶች እኔ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው በኩራት ተወጥረዋል። 19 ይሁንና ይሖዋ* ከፈቀደ በቅርቡ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜም እነዚህ በኩራት የተወጠሩ ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሳይሆን የአምላክ ኃይል ይኖራቸው እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ። 20 የአምላክ መንግሥት የወሬ ጉዳይ ሳይሆን የኃይል ጉዳይ ነውና። 21 ለመሆኑ የትኛው ይሻላችኋል? ዱላ+ ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ ልምጣ?

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ